የሞሮኮ ልዑካን ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አባቶች ጋር ተወያዩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የካቲት 16/2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) የሞሮኮ ልዑክ ከብፅዑ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት እና ከሌሎች የሃይማኖቱ አባቶች ጋር ውይይት አድርገዋል።

የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትንና ታሪካዊ ቦታዎችን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የልዑካኑ ቡድን በዛሬው የጉብኝት መርሐ ግብር ቤተክርስቲያኗ ከሃይማኖታዊ ተልዕኮ በተጨማሪ ሰብዓዊ ድጋፎችን ለማጠናከር የሚሠሩ ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

የትምህርት ፣ የጤና እና ሌሎች ማኅበራዊ ተቋማትን በማቋቋም ሰላም እንዲሰፍን እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የሰላም ክበባትን በተለያዩ ቁሳቁሶችን በመደገፍ እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ሰላምን ለማጎልበት ሰፋፊ ሥራዎችን እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

ሰላም ለኢትዮጵያ !