በኅብረ ብሔራዊ የፌዴራል ስርዓት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በኅብረ ብሔራዊ የፌዴራል ስርዓት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ

የካቲት 16/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር ከህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ጋር በመተባበር በኅብረ ብሔራዊ ፌዴራል ስርዓት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

ስልጠናውን በንግግር ያጠቃለሉት የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና መንግስታት ግንኙነት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንድማገኝ ሐይሌ የሰላም ሚኒስቴር ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር እና የፌዴራሊዝም ስርዓት እንዲጎለብት ለማድረግ በርካታ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በቀጣይም ይህን ተግባር ለማጠናከር ከከልሎች ጋር በትብብር 300ሺህ ለሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ይሰጣል ብለዋል፡፡

አቶ ወንድማገኝ ሐይሌ አክለውም ስልጠናው የፌዴራሊዝም ፅንስ ሃሳብ፣ በኢትዮጵያ የፌዴራል ስርዓት አተገባበር ስኬቶች፣ ተግዳሮቶች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የተሰጠ መሆኑን ገልፀው ለቀጣይ ስራዎች ግብዓት የተገኘበትም ነው ብለዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ክልል ከክልል እና ህዝብ ከህዝብ ጋር ያለውን ግንኙነት እና ትስስር ለማጠናከር ሰፋፊ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

በስልጠናው ላይ የሰላም ሚኒስቴር፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የክልል ምክር ቤት ተወካዮች፣ የዩኒቨርሲቲ ተወካዮች እና የሴቶች ማህበር ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡