ሰላም ከምንም ነገር በላይ ነው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ዋጋ ተመን የለውም፡፡ ፍጥረት ሁሉ ሰላም ያስፈልገዋል፤ ሁሉም ሰላምን ይሻሉ፡፡ ከየትኛውም ፍጥረት በላይ ለሰው ልጅ ደግሞ ሰላም ከምንም በላይ ነው፡፡ ሰላም ለሰው ልጅ የህልውና መሠረት ነው፡፡ ለህልውና አስፈላጊ የሚሆኑ ነገሮች በበቂ ሁኔታ ተሟልተው ሰላም ባይኖር ከንቱ ነው፡፡

ለሰላም ከፍተኛ ዋጋ የሚከፈለው እና ከነገሮች ሁሉ ሰላምን ለማስፈን የላቀ ጥረት የሚደረገው የሰላም ዋጋ ተመን የማይወጣለት እጅጉን የላቀ ስለሆነ ነው፡፡

የሰው ልጅ ለመኖር ውስጣዊ ሰላምም ሆነ ውጫዊ ሰላም ያስፈልጉታል፡፡ ሰላም ለሁላችንም የሚያስፈልገን፣ ሁላችን ልንጠብቀው የሚገባ፣ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ብናጣው እንኳ ሁላችንም በጋራ ጥረት ሠርተን የምንመልሰው ነው እንጂ በአንድ ወገን ጥረት ብቻ የሚጠበቅ አይደለም። ሁሉም በጋራ ዘብ የሚቆምለት የሁሉ ነገር መሠረት ነው፡፡

በመሆኑም ሰላም ከጥል፣ ከመለያየት፣ ከመጠላላት፣ ከመገፋፋት፣ ከመነቃቀፍ ተቆጥበን ተስማምተን እና ተግባብተን በመኖር የሚገለጥ ነው፡፡ ስለዚህ ሰላም ለሁሉ እንደሚያስፈልግ ካወቅን ውስጣዊና ውጫዊ ሰላምን የሚፈጥሩ ነገሮችን በማጎልበት፤ ሰላምን የሚገፉ አሉታዊ አመለካከቶችን እና ድርጊቶችን በመከላከል በሀገራችን ሰላም እንዲፀና በጋራ መቆም አስፈላጊ ነው፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ !