የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አምባሳደር ክቡር ሞሐመድ ሳሌም አል-ራሽዲን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ ዓለም ዓቀፍ የሃይማኖት ኮንፈረንስ የፓናል ውይይይ ተካሄደ
资产发布器
መስከረም 20/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፤ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አምባሳደር ክቡር ሞሐመድ ሳሌም አል-ራሽዲን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቅርብ ግንኙነት በማድነቅ የሰላም ሚኒስቴር በሰላም ግንባታ፣ሰላምን በሚያጠናክሩ እና በሚያጸኑ የተለያዩ ስራዎች ዙሪያ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር እንደዚሁም በወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት እያከተከናወኑ ያሉ ተግባራት ዙሪያ ገለጻ ያደረጉላቸው ሲሆን፤ በቀጣይም ሰላምን በሚያጠናክሩ ተግባራት በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መሰል ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀዋል።
ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) አክለውም ኢምባሲው ወደ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በመምጣት በመጎብኘታቸው አብሮነታቸውን እና ለጋራ ግንኙነቱ የሰጡትን ትኩረት አመስግነዋል።
ክቡር ሞሐመድ ሳሌም አል-ራሽዲን የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አምባሳደር በበኩላቸው ስለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የልማት ስራ በማድነቅ ሰላምን የማጽናት ስራው አካል በመሆን በወንድማማችነት እና በአብሮነት በመረዳዳት አብረው መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
访问最多的资产
እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም ዓቀፍ የሃይማኖት ኮንፈረንስ ላይ ''ሃይማኖታዊ አስተምሮዎች ለሰላም መስፈን ያላቸው ሚና እና በኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች ተከባብረውና ተዋደው ከመኖር አንፃር ያለው ልምድ ''አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሂዷል ።
በፓናል ውይይወቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፣ ዕስልምና እና ወንጌላዊያን ሃይማኖቶች ስለ ሰላም ያላቸው አስተምሮዎች እና እርስ በዕርስ ተከባብረው ከመኖር አንፃር ያላቸው ልምድ ቀርቦ ውይይት ተካሂደል፡፡
የፖናል ውይይቱን የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) መርተውታል።