Innehållspublicerare

null የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ አሰጠጣ ሥርዓት ለማዘመን የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ተሰጠ

መስከረም 8/2018 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር የአሠራር ሥርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅት ለመሥራት በሚቻልበት አቅጣጫ ከአጋር ድርጅቶችና ተቋማት ከተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል።

የሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ በሰጡት ማብራሪያ፡- ግጭት በሰው ልጅ መካከል በሚኖር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነት መሠረት አድርጎ ሊከሰት የሚችል ተፈጥረዊ ጉዳይ እንደመሆኑ ከመከሰቱ በፊት ቀድሞ መከላከል ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ጠቅሰው ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የግጭት ቅድመ መከላከል ሥርዓቱን በተደራጀና በዘመነ መንገድ በአጋርነትና በትብብር እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

 

የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂና ፈጣን ምላሽ አሰጣጡን የዘመነና በጥናት ላይ የተመሠረተ ለማድረግ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ሶፍትዌር የማበልፀግ እና በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የመረጃ ቋት (ዳታ ሴት) የመሥራት ፕሮጀክቶች ተጠናቆ ወደ ተግባር እየተገባ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ውጤታማነቱ የላቀ እንዲሆን በትብብር ለመሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለማሳደግ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑ ተገልጿል፡፡