በጎ ፈቃደኝነት ለሀገራችን እድገት

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

'' በጎ ፈቃደኝነት ለሀገራችን እድገት ''

የሰላም ሚኒስቴር የብሔራዊ የበጎ ፍቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት 5ኛ ዙር የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስልጠና መክፈቻ መርሀ ግብር ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ተካሂዷል።

የመክፈቻ መርሀ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሒሩት ደሌቦ ብቁ፣ ተወዳዳሪ እና መልካም ስብእናን የተላበሰ በጎ ፈቃደኛ ወጣት መፍጠር የመርሀ ግብሩ ዋነኛው አላማ ነው ብለዋል። አክለውም መርሀ ግብሩ በወጣቶች መካከል ጥላቻን በማስወገድ ወንድማማችነትን በማጎልበት ሀገራችን የጀመረችውን የእድገት ግስጋሴን በማገዝ ልእልናዋን ማስቀጠል መሆኑን ገልፀዋል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ በመክፈቻ መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን የብዙ ቋንቋ፣ ባህል፣ ትውፊት እና ታረክ ባለቤት ከሆነችው ኢትዮጵያ የተገኛችሁ የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት ሰልጣኝ ወጣቶች በምታካብቱት እውቀት በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች በመሰማራት የዜግነት ግዴታችሁን የምትወጡበት ነው ብለዋል። በተጨማሪም ወጣቱ አምራች ሀይል በማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃትና በቁርጠኝነት በመሳተፍ አርአያነታችሁን ማሳየት አለባችሁ በማለት አሳስበዋል።

በመጨረሻም ለሰልጣኞች የስልጠና ስነምግባር እና ደንብን በተመለከተ በተቋሙ ባለሙያዎች ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

በመርሀ ግብሩም ላይ የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች፣ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና የተቋማቱ ሰራተኞች ተሳትፈዋል።